በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ወደ አሜሪካ አመራ

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ ልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ መሄዳቸው ተገልጸዋል፡፡

የጉዞው ዓላማ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአማራ ልማት ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ለማስቻል እንደሆነ ከአማራ ብዙሓን መገነኛ ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልጸዋል፡፡   

ለውጡን ተከትሎ በክልሉ መንግስት አቋም ላይ በመወያየት በቀጣይ ስራዎች ላይ አብሮ ለመስራት ያለውን መልካም አጋጣሚ ማሳወቅም ሌላው ዓላማ ነው ብለዋል፡፡

ልዑኩ በሰሜን አሜሪካ በሚኖረው ቆይታ በተለያዩ ግዛቶች የአማራ ልማት ይመለከተናል ከሚሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ይመክራል፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ያላቸውን አንድነት በማጠናከር ታላቅነትን በጋራ የማስቀጠል ስራም ከውይይቱ ዓላማዎች መካከል ነው ተብሏል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ወደ አሜሪካ አቅንተው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡ (ምንጭ፡- የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት)