የስዊድን አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኝነት እንዲጎለብት ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የስዊድን አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት /SIDA/ በኢትዮጵያ ነፃ  ጋዜጠኝነት እንዲጠናከር  የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ይህ የልማት ድርጅት ነጻ ሚዲያን በኢትዮጵያ ለማጠናከር የሚያስችል ስልጠና ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ሰጥቷል፡፡

ከስልጠናው በኋላ የኤጀንሲው ተወካይ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ  ነጻ ሚዲያን ለመተግበር ጅማሮ ላይ ነች ብለዋል፡፡

የስዊድን መንግስትና ድርጅቱ ይህንን ጅምር ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆኑም አረጋግጠዋል፡፡

ሲዳ በኢትዮጵያና በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በርካታ የልማት ተግባራትን በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡

 ኢትዮጵያ እና ስዊድን የቆየና ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ስዊድን  እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ1946  የመጀመርያ የቆንስላ ጽ/ቤቷን በኢትዮጵያ ከፍታለች፡፡