የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ቀን በኢትዮጵያ በልዩ ሁኔታ እንደሚከበር ተመድ አስታወቀ

የዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ቀን በመጪው  ሰኞ  ዕለት  በኢትዮጵያ በልዩ  ሁኔታ እንደሚከበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት  አስታወቀ ።   

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ክልላዊ   ቢሮ  ተወካይ ነዋንኮላን ቬውዴ ኦባሆር እንደተናገሩት  ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ  መብት  ቀን በኢትዮጵያ  የመጡትን  አወንታዊ  ለውጦችን  በማሰብ  በመጪው   ሰኞ   በልዩ ሁኔታ   እንደሚከበር ገልጸዋል  ።       

የዓለም  አቀፉን  የሰብዓዊ መብት ቀን በዓልን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን  ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር  ጋር  በመተባበር የሚከበር  መሆኑም  ተገልጿል ።      

የኢትዮጵያ  ሰብዓዊ መብት  ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር በበኩላቸውን እንደገለጹት ቀኑ  የሰብዓዊ መብትን ማክበርን   በተመለከተ  ህብረተሰቡን  ግንዛቤ በማስጨበጥ  እንደሚከበር  ተናግረዋል ። 

በተጨማሪም  በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ቀን በዓል ላይ የተለያዩ  የመንግሥት  የሥራ ኃላፊዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ፣ የአገር  ሽማግሌዎች ፣  የኃይማኖት  አባቶች፣  የተባበሩት  መንግሥታት ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት የዲፕሎማሲ  ማህበረሰቦችና  ተወካዮች   ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

የዓለም አቀፉ  የሰብዓዊ መብት ቀን  መከበር  የአገር መሪዎች  ከተባበሩት  መንግሥታት  ድርጅት የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች    ጋር አብሮ  የሚሄድ  የሰብዓዊ መብት ህጎችንና  ፖሊሲዎችን  በማውጣትና እንዲሻሻሉ በማድረግ   የሰብዓዊ መብት አያያዝ ባህልን ይበልጥ  ማሳደግ  እንደሚገባቸው  ዶክተር አዲሱ  ተናግረዋል ።