በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂዴት እንዲኖር የድርሻቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገለጹ

በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂዴት እንዲኖር የድርሻቸውን እንደሚወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ገለጹ፡፡

ለዋልታ አስተያየታቸውን የሰጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቋሙ ያልተፈቱ በርካታ ጥያቄዎች ቢኖሩም ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ማቅረብና በውይይት ማመን ከተማሪዎች የሚጠበቅ ነው ብለዋል፡፡

ድንጋይ ከምወረውር ሰው ጋር በመሆን ድንጋይ በመወርወር አላስፈላጊ ግጭትና ሁኬት ውስጥ ከመግባት ለምን እንደምወረወር ራስን በመጠየቅ ምክንያታዊ መሆን ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡

ተማሪዎቹ ከጀርባ ያለውን ቤተሰብ በማሰብና ተምረው፤ ሳይማር ያስተማረውን ህብረተሰብ ለመጥቀም መሆን እንዳለበትም አክለዋል፡፡

በተጨማሪም በሰላማዊ መማርና ማስተማር ሂዴት በልዩነት ውስጥ ትክክለኛ የሃሳብ ፍጭት ኖሮ በሰላም ማስኬድ መቻል የሠለጠነ ሰው ባህል እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲ ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚመጡ ተማሪዎች መገኛ በመሆኑ የተለያዩ ብሔረሰብና ኃይማኖት ልዩነቶችን በማስተናገድ ተማሪዎቹ ተቻችለውና ተከባብረው መማማር እንደሚያስፈልግም ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡