በቤኒሻንጉል ጉምዝና በኦሮሚያ አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተጠረጠሩ አምስት አመራሮች ተያዙ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ ናቸው ያላቸውን አምስት የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ፖሊስ ግብረ ሀይል በዛሬው ዕለት ባካሄደው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ የክልሉ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊና የቀድሞ አሶሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚገኙበት ታውቋል ።

በፌዴራል ፖሊስ መግለጫ መሰረት ተጠርጣሪዎቹ በሰኔ 17ቱ የአሶሳ ከተማ ግጭት እንዲሁም በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አጎራባች አከባቢዎች ላይ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የችግሩ ጠንሳሾች ሆነው የተጠረጠሩ ሲሆኑ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ስር የማዋል ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል ።