ኢንጂነር አይሻ መሃመድ የአብዴፓ ሊቀ መንበር በመሆን ተመረጡ

አብዴፓ ሰሞኑን ሲያካሂድ በቆየው 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ኢንጂነር አይሻ መሃመድን የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ/አብዴፓ/ ሊቀመንበር በማድረግ  መረጠ ። 

አብዴፓ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ደግሞ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።

አብዴፓ በተጨማሪም የፓርቲውን 11 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫን አካሂዷል ። 

ከህዳር 23 ጀምሮ በሰመራ ሲካሄድ የቆየው የአብዴፓ 7ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባዔም ባለፉት አመታት በክልሉ በነበረው አፈፃፀም እና በወደፊት የልማት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት  በማድረግ  ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤው ተጠናቋል ።   

የአብዴፓ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ዝርዝር  እንደሚከተለው  ቀርቧል ።  

1.ኢ/ር አይሻ መሃመድ

2.አቶ አወል አርባ

3.አቶ ኢብራሂም ዑመድ

4.አቶ አህመድ ሱልጣን

5.ወ/ሮ ዘሃራ ዑመድ

6.አቶ መሃመድ ሃሠን

7.አቶ መሃመድ ጠይብ

8.አቶ ጣሃ አህመድ

9. አቶ ዓሊ ሁሴን ዌኢሳ

10. አቶ ኤላማ አቡበከር

11. አሊ ሁሴን ዑመር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመሆን ተመርጠዋል።