የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ነገ አስቸኳይ ጉባዔውን እንደሚያካሄድ ተገለጸ

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክርቤት አስቸኳይ ጉባዔውን በነገው ዕለት እንደሚያካሄድ  ተገለጸ  ።

የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢድሪስ መሐመድ እንደተናገሩት ጉባዔው ከነገው ዕለት ጀምሮ መካሄድ የሚጀምር ሲሆን አዋጅና ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።   

የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ጉባኤ በቅርቡ ባደረገው 7ኛው መደበኛ ጉባዔ ላይ ያደረገውን የአመራር ሽግሽግና ውሳኔዎች ተከትሎ እንደሚከናወን ገልጸዋል።

ነገ በሚጀመረው ጉባኤ  የክልሉን ርዕሰ መስተዳድርና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲሁም የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በአገር ደረጃ የተጀመረውን ለውጥ ወደ ክልሉ ለማውረድ የሕዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት የአስፈጻሚ አካሎችን አደረጃጀት ለመወሰን የወጣን ረቂቅ አዋጅ የክልሉ ምክር ቤት መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

የአፋር ብሔራዊ  ክልል መንግሥት  ምክር ቤት በአጠቃላይ 96 አባላት አሉት።