ፕሬዚደንት ሣህለወረቅ ዘውዴ በአፍረካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ቪየና ኦስትሪያ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሣህለወረቅ ዘውዴ በአፍረካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ቪየና ኦስትሪያ አቀኑ፡፡

በነገው እለት የሚካሄደው የአፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ትኩረት እንደሚሠጠው ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣህለወረቅ ዘውዴ በቆይታቸው ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስፋፋት በምታካሂዳቸው ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ ኩባንያ ኃላፊዎች ጋር ዉይይት እንደሚያደርጉም የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡