ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተለያዩ የፌደራል ተቋማት አዳዲስ ሹመቶች መሥጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1 አቶ ኃይላይ ብርሀኔ ተሰማ- የጠቅላይ ሚንስትሩ ብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣
2 ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ- የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር፣
3 አቶ ሳንዶካን ደበበ- የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣
4 ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዳይሬክተር፣
5 አቶ ተመስገን ጥላሁን- የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ም/ዋና ዳይሬክተር፣
6 አቶ ሙሉቀን ቀረ- የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር፣
7 አቶ ገብረመስቀን ጫላ- የኢትዮጵያ ካይዘን አንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተገልጿል ።