ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኦስትሪያ ቆይታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ በኦስትሪያ ቬና ‘’በዲጂታል ዘመን ትብብርን መፈፀም’’ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፎረሙ በአዳዲስ ግኝቶችና ዲጂታል ቴክኖሎጅ ልማት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተወያየ ሲሆን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት እያከናወነች ያለውን ተግባር በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

ፎረሙ የሁለቱን አህጉር ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በር የከፈተ መሆኑንም ፕሬዝዳንቷ በንግግራቸው ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ከተለያዩ አገራት መሪዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ ታላለቅ የኩባንያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውም ተገልጿል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት)