በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጠናከር ለማስቻል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ነዋሪዎች ገለጹ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጠናከር ለማስቻል የድርሻቸውን እንደሚወጡ በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች አረጋገጡ።

ነዋሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በተማሪዎች መካከል ግጭት እንዲፈጠርና ወደ ማህበረሰቡ እንዲዛመት የሚፈልጉ ሠራተኞቹን እንዲፈትሽም አሳስበዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ”መንስዔው ለጊዜው እየተጣራ ነው” በተባለው ሁከት የመማር ማስተማሩ ሂደት መስተጓጎሉን ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራውን ለመጀመር በዙሪያው ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ተወያይቷል ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ያሬድ ማሞ በነዋሪዎቹ የተነሱ ሃሳቦች ለዩኒቨርሲቲው ቀጣይ ሥራ ጠቃሚ በመሆናቸው ራሱን ለመፈተሸ እንደሚጠቀምባቸው ገልጸዋል፡፡

”በመረጃና ማስረጃ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፤ የሚደበቅና የሚድበሰበስ አንዳችም ነገር የለም” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡