ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ጋር ተወያዩ

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

በውይይቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ እና የሃገር ግንባታ ጉዞን እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

በቀጣይ የሁለቱ ሀገራት ትብብርና ቅንጅት የበለጠ ተጠናክሮ ለቀጠናው ሃገራት ሰላምና ዕድገት እንደሚሰሩ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩሱፍ ኪብር ተናግረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው የሁለቱ ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ታሪካዊ ከፍታውን ጠብቆ ለማጠናከር የኢትዮጵያን ዝግጁነት አንስተዋል።

በተለይ በቆዬው የህዝብ ለህዝብ ታሪካዊ መተሳሰር እና መተሳሰብ በንግድና ኢኮኖሚ የበለጠ እየዳበረ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትንቀሳቀስ አረጋግጠዋል። (ምንጭ፡-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት)