የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ በኢንተር ኮንቲነታል ሆቴል እየተካሄደ ነው።

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምክክር መድረክ ፥ ባለፈው ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተዘጋጅቶ የነበረው ውይይት 2ኛ ምዕራፍ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንደተናገሩት  ነጻ፣ ፍታዊና ታመዓኒ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችሉ የፖለቲካና የህግ ለውጦች ተከናውነዋል ብለዋል።

እንደ  ወይዘሪት ብርቱካን ገለጻ የዴሞከራሲ ተቋማትን ለመገንባት፣ በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊኖር የሚገባውን ትብብር ለማጠናከርና ተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው የጋራ ምላሽ ለመሥጠት የሚያስችሉ ሓሳቦችን ለማዳበር ምክክሩ አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

ፓርቲዎቹ በጽሑፍ ለምርጫ ቦርድ ያቀረቧቸውንና ወደፊትም የሚያቀርቧቸው አጀንዳዎችን የቦርዱ ሰብሳቢና ቦርዱ በሚያቋቁመው የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት በቅደም ተከተል ለውይይት አቅርበው ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ኤፍቢሲ)