ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቤጉህዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከቤንሻንጉል ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር በትላንትናው ዕለት በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታዎች ዙሪያ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የክልሉን የአስተዳደር እና የልማት ችግሮችን እንዲሁም የግጭትና አለመረጋጋት መንስኤዎችን ለመቅረፍ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

በሌሎች ክልሎች እንደታየውም አመራሮቹ በለውጥ እንቅስቃሴዎች ሰፊውን የክልሉን ነዋሪ በተለይም የክልሉን ወጣት አቅም በመጠቀም ወደ ክልል ደረጃ ለማውረድ ቃል ገብተዋል፡፡ (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)