ኦዲፒ እና ኦነግ የተስማሙባቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ቢቋቋምም አመርቂ ስራ አለመስራቱ ተገለጸ

የኦሮሞ ዴምክራሲያዊ ፓርቲ ኦዲፒ እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የተስማሙባቸውን ስምምነቶች ተግባራዊ የሚያደርግ ኮሚቴ ቢቋቋምም ስምምነቶቹን ተግባራዊ ለማድረግ የተኬደበት ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡

ኦዴፓ እና ኦነግ ካለፈው ህዳር 16 አንስቶ በተስማሙባቸው ስምምነቶች ተግባራዊነት ላይ የሚሰራና ከሁለቱም ወገን የተውጣጡ ስድስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ማቋቋቸው ይታወሳል፡፡

ይህ ኮሚቴ በሁለቱም ወገኖች የተደረሱ ስምምነቶች ተግባራዊ የማድረግ፣ ስምነቶቹን ለህዝብ ይፋ የማድረግ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበርና የልማት ተግባራት እንዳይቋረጡ የማስቻል ስራዎችን እንዲሰራ ታልሞ ነበር የተቋቋመው፡፡

ይሁን እንጂ ኮሚቴው እቅድ አዘጋጅተው ወደ ስራ ቢገባም የሚፈለገውን ተጨባጭ ተግባር ሳያከናውን ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

በዚህ ኮሚቴ ውስጥ ከኦዴፓ የተወከሉት አቶ ሞገስ ኢዳው እንደገለጹት ኦነግ በክልሉ ያሉትን አባላት አወያይቼ ለመጨረስ አልቻልኩም በማለቱ ኮሚቴው የተቋቋመበትን አላማ ከግብ ማድረስ አልቻለም፡፡