የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዉዲ አረቢያ ማረሚያ ቤት ታስረው የቆዩ 451 ዜጎች መመለሱን አስታወቀ

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳዉዲ አረቢያ ማረሚያ ቤት ታስረው የቆዩ 451 ዜጎች መመለሱን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በጄዳ፣ በጂዛን እና አከባቢዋ በተለያዩ ጉዳዮች ተከሰው በእስር ላይ የቆዩ 451 እስረኞች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ነው ያስታወቀው፡፡

ትላንት በታህሳስ 16፤2011 ዓ.ም በሳዉዲ አረቢያ መንግስት ምህረት ተደርጎላቸዉ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የዲፕሎማሲ ማግባባት ስራ መሰራቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ባለፈዉ ሳምንትም ወደ 2 ሺህ 400 የሚሆኑ ዜጎችን ከሳዉዲ አረቢያ፤ 231 ዜጎችን ደግሞ ከታንዛኒያ መመለሳቸዉ ይታወቃል። (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)