ቡራዩ ተገኙ የተባሉት ሂሎኮፕተርና አውሮፕላን ለመማርና ማስተማር ተፈልገው የተቀመጡ መሆናቸው ሜድሮክ አስታወቀ

የሜድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ በሆነው ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ ተገኙ የተባሉት ሄሌኮፕተርና አውሮፕላን ለመማር ማስተማር አገልግሎት የተቀመጡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ በስጋት ሊመለከታቸው እንደማይገባ ሜድሮክ ኢትዮጵያ አስታወቀ።        

በሜድሮክ ኢትዮጵያ እህት ኩባንያ ዩኒቲ ዩንቨርሲቲ ቡራዩ ገፈርሳ ካምፓስ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የተቀመጡ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ሄሊኮፕተርና የእርሻ መድኃኒት መርጫ አውሮፕላን ለመማር ማስተማር አገልግሎት የተቀመጡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ በስጋት ሊመለከታቸው እንደማይገባ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አረጋ ይርዳው ተናግረዋል፡፡

ሜድሮክ ኢትዮጵያ በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ያስቀመጠው እኤአ የካቲት 17 ቀን 2008 በሱዳን እርሻ ጣቢያ ላይ ተከስክሶ የነበረው ቱርቦ ተርሸት ኤኬኤን የተባለው አገልግሎት  የማይሠጥ  ሄሊኮፕተር  መሆኑን  ዶክተር አረጋ ገልጸዋል ።

ሌላው አሮጌ አውሮፕላን የካቲት 25 ቀን 2017 በቦሌ ዓለም አቀፍ አየርማሪፊያ የመከስከስ አደጋ የደረሰባት የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ ኢት-ኤ.ኤም.አር የተባለ የንግድ አውሮፕላን ሲሆን ይህም ለቴክኖሎጂ ተማሪዎች መማሪያ እንዲሆን ተብሎ በዩኒቨርስቲው ግቢ መቀመጡን ዶክተር አረጋ አስረድተዋል ።

በዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ገፈርሳ  ካምፓስ ቅጥር ገቢ ውስጥ ሸራ ለብሰው የተቀመጡትን አገልግሎት የማይሠጡ ሂሊኮፕተርናአውሮፕላንን በተመለከተ ሰሞኑን የቡራዩ አካባቢ ነዋሪዎች ለቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጥቆማ  በማድረጋቸው ጉዳዩን  በማጥራት  ሥራ ላይ እንደነበር ተገልጿል ።