የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ካርቱም ገቡ

​​​​​​የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በዛሬው እለት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ሱዳን ካርቱም ገብተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ ካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦሳማ ፈይሰል አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሚኒስትሩ በካርቱም ቆይታቸው ከሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሸ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡ (ምንጭ፡-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት)