በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የተቋማት አመራሮች ከተማሪዎች ጋር ተቀራርበው ሊሠሩ ይገባል

በተለያዩ ዩኒቨርሰቲዎች የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የዩኒቨርስቲ አመራሮች ከተማሪዎች ጋር  ተቀራርበው ሊሠሩ ይገባል  ተባለ ።

የተለያዩ  ዩኒቨርስቲዎች መምህራንና አመራሮች ለዋልታ ቴሌቭዠን በሠጡት አስተያየት እንደገለጹት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ  የሚፈጠሩ ችግሮች ውስጥ የሚሳተፉት ጥቂት ተማሪዎች  ብቻ  መሆናቸውንና  በአብዛኛው ጊዜ ተማሪዎች  የሚያነሱት  ጥያቄዎች  የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን  ናቸው ብለዋል ።  

በጅማ ፣ አዲስ አበባ ፣ ወልዲያ፣ ኮተቤና ወሎ ዩኒቨርስቲዎች አመራራሮችና መምህራን ለዋልታ እንደገለጹት  ጥቂት ተማሪዎች የተለያዩ ፍላጎት ያላቸው አካላትን ዓላማ ለማስፈጸም በሚያስችሉ  አጀንዳዎች ላይ ሲጠመዱ ታይተዋል  ብለዋል ።

እንደ አመራሮቹ ገለጻ  አብዛኛዎቹ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹ የሚያነሱት ጥያቄዎች ከምግብ አቅርቦት ፣ ከቤተ መጽሐፍትና ሌሎች  አገልግሎት  መጓደል ጋር  የተያያዙ በመሆናቸውንና የሚያጋጥሙ ችግሮችን የተቋማቱ ኃላፊዎች ከተማሪዎቹ  ጋር  በመሆን  ሊፈቱት  የሚገባ ነው ።

በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሌላ አጀንዳ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ተማሪዎች የሌሎች  ሰላማዊ ተማሪዎች ትምህርትን  እንዳይስተጓጉሉ  ተቀራርቦ  መሥራት  እንደሚያስፈልግም  አመራሮቹ በሠጡት አስተያየት ጠቁመዋል።

በዩኒቨርስቲ የሚማሩ ተማሪዎች ጥያቄዎቻቸውን በሰላምና በተረጋጋ  ሁኔታ እንዲያቀርቡ  የአምስቱ  ዩኒቨርስቲዎች አመራሮችና መምህራን  ጥሪ አቅርበዋል ።