ፍርድ ቤቱ አብዲ መሐመድ ኡመርና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ ለማድረግ የ14 ቀን ጊዜ ፈቀደ

ፍርድ ቤቱ አብዲ መሐመድ ኡመርና ሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ ፖሊስ  የጠየቀውን የ14 ቀናት ጊዜ  ፈቀደ ።

መርማሪ ፖሊስ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ችሎት ቀደም ሲል በጅምላ የተቀበሩ ሰዎችን ከቦታው አንስቶ በክብር እንዲያርፍ የማድረግ ሥራዎችን ለማከናወን  ተጨማሪ ጊዜ  እንደሚያስፈልገው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል ።

ፖሊስ  እያደረገ  ባለው  ምርመራ  በጅምላ ተገድለው  ተቀብረዋል የተባሉ 200 ሰዎችን  በተመለከተ   ተጨማሪ  የሰዎች  የቃል ምስክርነትን    ለመሰብሰብ  ተጨማሪ ቀናት  አስፈላጊ መሆኑንም ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል ።