ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአየርላንድ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በኢትዮጵያና አውሮፖ መካከል ያለውን የጠነከረ ግንኙነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአየርላንዱ መሪ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ወራት የተመዘገቡትን ለውጦች አድንቀው አገራቸው ለኢትዮጵያ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

ይህ ይፋዊ የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል ያለውን ከ20 አመታት በላይ የዘለቀ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ይታመናል ተብሏል። (ምንጭ፡-የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት)