በሁመራ ከተማ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች በሁመራ ከተማ የህዝብ ለህዝብ መድረክ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ በሺህዎች የሚቆጠሩ የኦምሓጀርን ነዋሪዎች ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት የመካላከያ ኃይል አባላት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ተገኝተዋል፡፡

በዚሁ መድረክ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ተገኝተዋል፡፡

የህዝብ ለህዝብ መድረኩ በኢትጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል የተጀመረውን ሰላማዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ተግልጿል፡፡

ከሦስት ቀናት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኘውን የሁመራ-ኦምሓጀርን መንገድ መክፈታቸው ይታወሳል፡፡ (ኤፍ.ቢ.ሲ)