ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር ይወያያሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከፍተኛ አመራሮች እና በዓለም ዙርያ በተለያዩ ሚሲዮኖች ኢትዮጵያን ከሚወክሉ ከስድሳ በላይ አምባሳደሮች ጋር በሚቀጥለው ሰኞ ጥር 6፣2011 ዓ.ም. እንደሚወያዩ ተገለፀ።  

ከተለያዩ ሀገራት የተጠሩ 60 የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር በሚቀጥለው ሳምንት ውይይት ይካሄዳል::

በውይይቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተከናወነው የአደረጃጀት እና ሌሎች የሪፎርም ስራዎች፣ ያንን ተከትሎ ስለመጡ የዲፕሎማሲ ስኬቶች እንዲሁም የዳያስፖራ ተሳትፎ እና የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ስራዎች ግምገማ ይደረግባቸዋል።

ዛሬ ቀደም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በነበሩት አምባሳደር መለስ አለም ምትክ አቶ ነብያት ጌታቸው መሾማቸው ይፋ ሆኗል።

አዲስ የተሾሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በዛሬው እለት በተለያዩ ጉዳዮች ላይም መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የፊታችን ጥር 4, 2011 ዓ.ም የባህል ቀን እንደሚከበር አስታውቀው፥ በባህል ቀኑ ላይም በአፍሪካ ህብረት የሚገኙ አምባሳደሮች እንዲገኙ ይደረጋል ብለዋል።

በመርሃ ግብሩም በዋናነት አምባሳደሮቹ አዲስ አበባን ለማስተዋወቅ የማስጎብኘት ተግባራት እንደሚከናወኑም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።