የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

ፓርቲዎቹ አሁን ያለውን የፖለቲካ አሠላለፍ ታሳቢ ያደረገ የሁለትዮሽ ውይይት በሥራ አሥፈጻሚዎቻቸው በኩል ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተገናኝተው አድርገዋል።

በምክክር መድረኩም ከአዴፓ 11 የሥራ አሥፈጻሚ አባላት የተገኙ ሲሆን፥ በአብን በኩል ደግሞ 9 የሥራ አሥፈጻሚ አባላት ተሳትፈዋል።

በዚህም መሠረት ሁለቱ ፓርቲዎች፥ በጸጥታ ጉዳይ፣ በሠላምና ደህንነት፣ በልማትና የአማራ ህዝብ የጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት በሁለቱም ፓርቲዎች በኩል በተመረጡ ሥራ አሥፈጻሚዎች በኩል የጋራ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

ከሁለቱ ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚዎች የተመረጡት የጥምር ኮሚቴው አባላት ወደ ፊት ዝርዝር ጉዳዮችን የሚያሳውቁ መሆኑን ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 (ኤፍ ቢ ሲ)