የአዴፓ ወጣቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዳማ ከተማ ተጀምሯል

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ ተጀምሯል።

በጉባኤው ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ጦይባ ሀሰንን ጨምሮ በርካታ የድርጅቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

ጉባኤው የወጣቶች አንድነት ለመሰረታዊ ለውጥ በሚል መርህ እየተካሄደ ይገኛል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፥ በየደረጃው የሚገኙ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳታፊዎች ናቸው።

ድርጅቱ በወጣቶች ጥረት ታግዞ ሀገራዊ ለውጥ ማምጣት እንደቻለ እና እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ድርጅት ለመጣው ለውጥ የግንባር ቀደምነት ሚና እንደነበረው በጉባኤው ላይ ተገልጿል።

የማህበራዊ ሚዲያ ትሩፋቶችን ለሀገር እድገት እና ለህዝቦች አንድነት መጠቀም እንደሚገባም በጉባኤው ተነስቷል።(ምንጭ:የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት)