በድሬዳዋ ከተማ ግጭት በመቀስቀስ የተጠረጠሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ ገለጸ

በድሬዳዋ ከተማ ግጭትን በመቀስቀስ የተጠረጠሩ 84 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።

የድሬዳዋ ፖሊስ ገለጻ፥ የጥምቀት በዓል ማግስት ጥር 13 ቀን 2011ዓ.ም የእግዚአብሔር አብ ታቦትን አስገብተው በሚመለሱ ምዕመናኖች ላይ ድንጋይ መወርወሩን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭትና ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች ናቸው በቁጥጥር ሥር የዋሉት።

እስከ አሁንም 84 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ በምርመራ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

ችግሩ ተከስቶ በነበረበት 09 ቀበሌ የቀደመው ሰላም ሙሉ ለሙሉ ወደ ነበረበት እየተመለሰ እንደሆነም ተገልጿል ። ( ምንጭ: የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን)