በቅርብ ጊዜያት በኢትዮጵያ የተከሰቱት ግጭቶች በፖለቲካና ሌሎች ኃይሎች ጣልቃ ገብነት የተፈጸሙ መሆናቸው ተገለጸ

በቅርብ ጊዚያት በአገሪቱ የተከሰቱ ግጭቶች በተለያዩ ፖለቲካዊና ሌሎች ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ምክንያት  የተፈጠሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሻል አንትሮፖለጂ ትምህርት ዘርፍ መምህር የሆኑት ዶክተር ኬረዲን ተዘራ ገለጹ።   

ዶክተር ኬረዲን ተዘራ ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹትየሽምግልና እሴቶችን  በአግባቡ የመጠቀም ልምድ  እየተቀዛቀዘ  በመምጣቱ በአገሪቱ እየተከሰቱ  ያሉትን  ግጭቶች  በቀላሉ  ለመፍታት አጋዳች አድርጎታል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአገሪቱ የሽምግልና  እሴቶችን  ከየትኛውም  ፖለቲካዊ ጫና ተላቀው  እንዲንቀሳቀሱ  በመፍቀድ  ሁሉም  የበኩሉን  ሚና  መጫወት እንደሚገባውም ዶክተር ኬረዲን አስገንዝበዋል ።

በመንግሥትና በሌሎች አካላት መካከል የሚፈጠሩ ያለመግባባቶችን  ለማስወገድም  በኢትዮጵያ ውስጥ  ያለውን የሽምግልና እሴትና ፀጋዎችን  በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያ እንደሌሎች በርካታ አፍሪካ  አገራትም በቅኝ አለመገዛቷ በራሱ ብርቅዬ የሆኑ ባህላዊ እሴቶቿን ከትውልድ  ወደ ትውልድ ማስተላለፍ እንድትችል አግዟል ብለዋል ዶክተር ኬረዲን  ።