ጠ/ሚ ዶክተር አብይ ከሶማሌ ክልል ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ዑመር ጋር ተወያዩ።

ከምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪም የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አህመድ ሽዴም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በክልሉ እየተካሄዱ ባሉ የልማት ስራዎችና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ነው የተባለው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም የክልሉን ልማት ማጠናከር የሚያስችል አቅጣጫ ሰጥተዋል።