ፍርድ ቤቱ የፍርድ መጓተትን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍርድ መጓተት ችግሮችን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ወደ 2 ሺህ 360 የዘገዩ መዝገቦችን እስከ ሚያዚያ 30 ለማጥራት አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ በላቸው አለሽሶ ለዋልታ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት ህብረተሰቡ ፍትህን በተፈለገው መጠን ባለማግኘቱ፣ የሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለመሸርሸራቸው ተጠያቂው ሁሉም የፍትህ ተቋማት ናቸዉ፡፡

የሙያውን ሽፋን በመጠቀም ፍትህን በሚያዛቡ ዳኞች ላይ እርምጃ የሚወስደው የዳኞች አሰራር ጉባኤ ይሆናል ነዉ ያሉት፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የኔነህ ስመኝ በበኩላቸው መፍትሄው ችግሮች ላይ በግልጽ መነጋገር እና ለመፍትሄውም መሰራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

የፍትህ ሥርዓቱን በዘላቂነት ለማስፈን ከዳኞች አሰራር ጉባኤ ጠንካራ ስራ በተጨማሪ የህብረተሰቡ አስተማማኝ ማስረጃ አቅራቢነት ወሳኙን ሚና የሚጫወቱ መሆኑን ነዉ የተገለፀው፡፡