በቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲሁም ምርጫ ላይ ሚዲያዎች በከፍተኛ ሃላፊነት ሊሰሩ ይገባል ተባለ

በቀጣዩ የህዝብና ቤት ቆጠራ እንዲሁም በ2012ቱ ሃገራዊ ምርጫ ላይ ሚዲያዎች በከፍተኛ ሃላፊነት ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡

ሚዲያ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያለውን ሚና በሚለከት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣የመንግስትና የግል ሚዲያ አመራሮችና ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ፣ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና እና አቶ ንጉሱ ጥላሁን የውይይት መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

አክቲቪስት ጃዋር በስርዓት ሽግግር ወቅት የሚዲያ ሚና፤ ጋዜጠኛ ሲሳይ የሚዲያ ሚና በሃገር ግንባታ እንዲሁም አቶ ንጉሱ የሚዲያ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ በሚሉ ርዕሶች ላይ ጽሁፍ አቅረበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም የሃገር ውስጥ ሚዲያዎች የተፈጠረውን ሰፊ የፖለቲካ ምህዳር በመጠቀም ያለባቸውን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

ሚዲያዎች ተቀራርበው የሚሰሩበት የሚዲያ ካውንስል እንዲቋቋምም ተጠይቋል፡፡

የሚዲያ ነጻነት እና የመረጃ ተደራሽነትን ይበልጥ ለማሻሻል መንግስት መንግስት ሊሰራቸው የሚገባቸው ስራዎች እንዳሉም ተጠቁሟል፡፡