አብን መንግስት የዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቅ ጠየቀ

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚፈጠሩ ግጭቶች ዜጎች ያለጥፋታቸዉ ለእንግልት ተዳርገዋል ብሏል፡፡

ለዜጎች እንግልት መዳረግ መንግስት  በአግባቡ ህግ የማስከበር ስራ አለመስራቱ ቀዳሚዉን ድርሻ ይወስዳል ያለዉ ንቅናቄዉ መንግስት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብሏል፡፡

አዲስ አበባ የሁሉም ኢትጵያዊ ከተማ ነች ስትሆን የከተማዉ ህዝብም በፈለገዉ መንገድ የመደራጀት መብቱ ሊከበርለት ይገባል ይላል፡፡

ንቅናቄዉ ኮንጨራን ጎራዴን በመያዝ ህጋዊ ዉሳኔን ለማስቀልበስ የሚደረግ እንቅስቃሴን በፅኑ እንደሚቃወመዉ ተናግሯል፡፡  

 ባለፉት ቀናት በተካሄደዉ የፓርቲዎች የቃል ኪዳን ፊርማ ስነ ስርአት ላይ ጠቅላይ ሚንስቴሩ “ለአንድ ክልል ብልን ህገ መንግስት አናሻሽልም” ያሉትን ንግግር ንቅነቄዉ ከአንድ ጠቅላይ ሚንስቴር የማይጠበቅ ነዉ ያለ ሲሆን አሁንም ወደፊትም ህገመንግስቱ የአማራን ህዝብ የማይወክል መሆኑን የሚያምንና እንዲሻሻልም እሰራለሁ ብሏል፡፡

አብን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙም ተገቢ መሆኑን ተናግሯል፡፡