የፌዴራል ዳኞች አስተዳዳር ጉባኤ ላይ ማሻሻያ ሊደረግ መሆኑን ተገለፀ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፣ አደረጃጃት እና የአሰራር ችግሮችን ለይቶ መፍትሄ መስጠት የሚያስችል ስራ ተጀምሯል፡፡

ረቂቁን ለማሻሻል ሶስት ንኡሳን ኮሚቴን ያቀፈ 17 የህግ ባለሞያዎች መካተታቸዉን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ገለፁ፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ እንደተናገሩት ወደ ፊት ተሻሽሎ እንዲጸድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚላከው አዋጅ እየቀረቡ ባሉ ሀሳቦች ዳብሮ እንደሚዘጋጅ ነዉ፡፡

በተያየዘም ተሻሽሎ የሚጸድቀው አዲስ አዋጅ በቀጣይ በፍትህ ረገድ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች በመቅረፍ በህግ የበላይነት የሚያምን ማህበረሰብ ለመገንባት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

አሁን በስራ ላይ የሚገኘው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አዋጅ 684/2002 ዓ.ም. ዘጠኝ አመታትን አስቆጥሯል፡፡

አዋጁ ከአባላት ቁጥር አንስቶ ግልጽ አንቀጾችን አለማካተትና በአሰራርና አደረጃጀት መቀረፍ የሚገባቸው አያሌ ክፍተቶች እንዳሉበት ሲነሳ ቆይቷል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ግብዓት እንደሚገኝበት የታመነ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ የህግ ባለሞያዎችና ጠበቆች፣ የቀድሞ የፌዴራል ፍርድ ቤት የበላይ አመራሮች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት መድረክ ተካሄዷል፡፡