ጠ/ሚ አብይ አህመድ ቤጂንግ ገቡ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቤጂንግ ቻይና ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚያዚያ 17 እስከ 19/2011 በቤጂንግ በሚካሄደው የ"ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ፎረም" ላይ ለመሳተፍ ነው ቻይና የገቡት።

ከአምስት አመት በፊት የተጀመረው ይህ ፕሮጄክት ሃገራትን በትራንስፖርትና በመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ለማገናኘት ያለመ ነው።

ቻይናም በፕሮጄክቱ አብረው በትብብር የሚሰሩ የማዕቀፉ አባል ሀገራትን በተጨባጭ የሚጠቅም መሆኑን ትገልጻለች።

የመጀመሪያው የፕሮጄክቱ ፎረም ከሶስት አመት በፊት የተካሄደ ሲሆን፥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ይሆናል።