ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ::
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራርንና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ ቻይና ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል::
በውይይቱ ወቅትም እስከ የፈረንጆች 2018 መጨረሻ ያለው የኢትዮጵያን የተጠራቀመ የብድር ወለድን ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘ አስታውቀዋል::
በተጨማሪም የቻይና መንግሥት የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክትን ጠቀሜታ ይረዳል ያሉት ፕሬዝዳንት ዥንፒንግ ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል::
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ሁለቱም መሪዎች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር በተለያዩ ዘርፎች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል::