ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሁለተኛው ቤልት ኤንድ ሮድ የመሪዎች ውይይት መድረክ ጎን ለጎን ነው ከቭላድሚር ፑቲን ጋር የተወያዩት፡፡

መሪዎቹ በሀገራቱ መካከል ስላለው ታሪካዊ ትስስርና በሌሎችም የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሩሲያ ፌዴሬሽን ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጋብዘዋቸዋል።