የኦሮሚያና የሱማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ የግንኙነት መድረክ ነገ ይደረጋል

የኦሮሚያ ክልልና የሱማሌ ክልል የህዝብ ለህዝብ የግንኙነት መድረክ በነገው ዕለት በአዳማ ከተማ እንደሚደረግ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ገለጹ፡፡

መድረኩ በኦሮሚያ ክልልና በሱማሌ ክልል ህዝቦች መካከል የነበረውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑን የገለጹት አቶ አድማሱ የኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች ጋር የሚያደርገው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከሱማሌ ክልል ወደ አዳማ የሚመጡ እንግዶች ዛሬ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ላይ አቀባበል ይደረግላቸዋል ነው ያሉት፡፡

የኦሮሚያ ክልል ከቤኒሻንጉልና ከአማራ ክልሎች ጋር የጀመረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከሶማሌና ከሌሎች ክልሎች ጋር እንደሚቀጥልም አቶ አድማሱ ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የፌዴራል መንግስት ተወካዮች፣ የክልል አመራሮችና የክልሎቹ ህዝቦች ተወካዮች ይገኛሉ ተብሏል፡፡