በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው

በሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር፣ ምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ራያ ቆቦና ሌሎችም አካባቢዎች ሲከሰቱ የቆዩ የፀጥታ መደፍረሶችና በተለይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ከሰሞኑ የተቀሰቀሰው ግጭት ያስከተለው ሞትና መፈናቀል ምክንያት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፡፡

በሠላማዊ ሠልፈኞቹ ‹‹የአማራ መገደልና መፈናቀል ይቁም፤ መንግሥት የዜጎችን ደህንነት ይጠብቅ›› የሚሉና የተለያዩ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።

ሰላማዊ ሰልፉ በደብረ ታቦር፣ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ መርዓዊና በሌሎች ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።

(ምንጭ ፦ አብመድ)