የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በድርጅታዊና ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ኮሚቴው ለስብሰባው በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ በመወያየት ቀጣይ የማሻሻያ ስራዎችን በተመለከተ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥምይጠበቃል፡፡/የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት/