የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ወደ ጁባ አቀኑ

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው በ67ኛው የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ለመሳተፍ ዛሬ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ አቅንተዋል።

ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ልዩ ሰብሰባ በደቡብ ሱዳን ተደራዳሪ ወገኖች የተደረሰው ስምምነት አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃ በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ነው የተባለው።

(ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት)