አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች አዲስ ፓርቲ ለመመስረት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ገለጹ

በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ሲታገሉ የነበሩ  አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ራሳቸውን በማክሰም ህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” የተባለ አንድ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት ዝግጅታቸውን መጨረሳቸውን አስታወቁ፡፡

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ሽግግር)፣ ኢትዮጵያችን ህዝባዊ ንቅናቄ (ኢትዮጵያችን)፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ቱሳ)፣ የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት (ኦህዲን) እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት (አረንጓዴ ኮከቦች) የከሰሙ ፓርቲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የአገሪቱ ህገ- መንግስትና የምርጫ ህጎችን በመከተል 7 ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚካተቱበት ይሆናል ተብሏል፡፡

የፓርቲው ምስረታ በመጪው ሀሙስ ይፋ ይደረጋልም ተብሏል፡፡