ወጣቱ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ

ወጣቱ ትውልድ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡

የአዲስ አበባ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮና ብራቩራ አፍሪካ ያዘጋጀው የሰላም ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ከተለያዩ አካባቢ የተውጣጡ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፣ የተለያዩ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ሰላም ወሳኝ በመሆኑ በየአካባቢው እየተከሰቱ ያሉ የሰላም እጦቶች ለመፍታት ወጣቶች ጉልህ ሚና ስላላቸው የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠይቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ የኢትዮጵያንና የተለያዩ ሀገራትን የሰላም ምልክት የሚያሳይ አርማ ለማስቀመጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡