የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ጅቡቲ አየር ማረፊያ ሲደርሱም በአገሪቱ አቻቸው ሞሃመድ አሊ የሱፍና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አቶ ገዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሆኑ ወዲህ ጅቡቲን ሲጎበኙ የመጀመሪያቸው ሲሆን፣ በቆይታቸውም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሁለትዮሽ ምክክሮችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ማምሻውን ወደ ጅቡቲ ማቅናታቸውን ከውጭ ጉዳይ ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡