ኢትዮጵያን እየገጠማት ካለው ችግር ለመታደግ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንሰራለን- የትግራይ ክልላዊ መንግስት

ኢትዮጵያን እያጋጠማት ካለው ችግር ለማዳን የትግራይ ሕዝብ ዛሬም እንደ ትላንቱ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጋር በጋራ በመሆን እንደሚታገል የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት 28ኛውን የግንቦት 20 በዓል ምክንያት በማድረግ ባወጣው የአቋም መግለጫ እንዳስታወቀው ኢትዮጰያ በደርግ ስርዓት ወቅት በዓለም በድህነታቸው በግንባር ቀደምትነት ከሚታወቁ 10 ሃገራት መካከል አንዷ ነበረች።

ከለውጡ በኋላም በኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተባበረ ትግል በዓለም የተፋጠነ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ 10 ሃገራት ተርታ መሰለፏዋንና ላለፉት 15 ዓመታትም በዚሁ መቀጠሏን መግለጫው አመልክቷል።

ሆኖም ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ግን በግንቦት ሃያ የተገኘው የፌደራል ስርዓት እየተሸረሸረ እና የህግ የበላይነት እየጠፋ በመምጣቱ ምክንያት ኢትዮጵያ አደጋ ላይ መድረሷን አስታውሷል።

ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዛሬም እንደትናንቱ የጋራ ትግላቸውን በማቀጣጠል ከችግሩ ለመውጣት በጋራ መስራት እንደሚገባቸውም ነው የክልሉ መንግስት መግለጫ ያመለከተው። (ኢዜአ)