ኢትዮጵያና ኤርትራ የሸንገን የሰላም ሽልማት ተበረከተላቸው

ኢትዮጵያና ኤርትራ የሸንገን የሰላም ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሽልማቱ ሁለቱ ሃገራት ወደ ሰላማዊ ግንኙነት በመመለስ ለወሰዱት ገንቢ እርምጃና በሰላም ዙሪያ ላደረጉት አስተዋጽኦ የተበረከተ ነው።

የሰላም ሽልማቱ በሉግዘምበርጉ የሰላም ሽልማት ኮሚቴ ሸንገን የሰላም ፋውንዴሽን አማካኝነት ነው የተበረከተላቸው።

ሽልማቱን በኢትዮጵያ በኩል በቤልጂየም፣ ሉግዘምበርግ፣ በአውሮፓ ህብረትና በባልካን ሃገራት የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ግሩም አባይ ተቀብለዋል።

በኤርትራ በኩል ደግሞ በአውሮፓ ህብረት፣ በቤልጂየም፣ ኔዘርላንድስ እና ሉግዘምበርግ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነጋሲ ካሳ ተቀብለዋል።

ተቋሙ በጋዜጠኝነት፣ ለሰላም አስተዋጽኦ ባደረገ የቴክኖሎጂ ፈጠራና ከሰላም ጋር በተያያዘ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሽልማት ያበረክታል መረጃዉ ያገኘነዉ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነዉ።