ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

ዶክተር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሹመትን አፅድቋል።

በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ ከቀረቡት 88 እጩዎች ውስጥ ዶክተር ዳንኤልን በቀለ ባላቸው የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው እንዲሾሙ አፅድቋል።

ዶክተር ዳንኤልን በቀለ ሹመቱ የተሰጣቸውም ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆነን ሲያገለግሉ የቆዩትን ዶክተር አዲሱ ገብረ እግዚአብሄርን በመተካት ነው። መረጃው የኤፍቢሲ ነው፡፡