በሰላም አስፈላጊነትና ምንነት ዙሪያ ያተኮረ ሥልጠና ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰላም አስፈላጊነትና ምንነት ዙሪያ ያተኮረ ሥልጠና ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ነው፡፡፡

የከተማዋ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከተማዋ ለሚገኙ ከ500 በላይ ሰላም በማስፈን ድርሻ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአሰልጣኞች ሥልጠና ነው እየሰጠ የሚገኘው፡፡

የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ፍሰሃ ጋረደው ከተማዋ የሀገሪቱ፣ የአፍሪካ እንዲሁም የዓለም መዲና በመሆኗ ሰላምና ጸጥታዋን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡  

በከተማው ዘላቂ ሰላም እንዲኖርም ህብረተሰቡን አሳታፊ ያደረገ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ዋልታ ያነጋገራቸው የሥልጠናው ተካፋዮች በበኩላቸው ሰላም የመኖራችን ህልውና እና የሁሉ ነገር መሠረት በመሆኑ መጠበቅ ይገባል ብለዋል፡፡

በተለይም ህብረተሰቡ የመደማመጥ ባህሉን ማዳበር እንደሚገባውም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡