የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና ዕጩ ርዕሰ መስተዳድር ሰየመ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር እና አቶ ተመስገን ጥሩነህን ደግሞ ዕጩ ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ መርጧል።

በተጨማሪም አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አገኘው ተሻገር የአዴፓና የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከዚህ በፊት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ዋና ዳይሬክተር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ማገልገላቸው ይታወቃል።

አቶ አገኘሁ ተሻገር ደግሞ የቀድሞው ሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የአማራ ሥራ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር፣ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ማገልገላቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ የክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ሆነዋል፡፡