ጠ/ሚ ዐቢይ የኩዌት ኤሚር ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኩዌት ኤሚር ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ አቅርበዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከኩዌት ኤሚር ሼክ ሳባህ አል አህመድ አል ጃበር አል ሳባህ ጋር በኩዌት ተወያይተዋል።

በቆይታቸውም አቶ አህመድ ሺዴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክትን ለኩዌት ኤሚር ሼክ ሳባህ አል አህመድ አል ጃበር አል ሳባህ አስረክበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የላኩት መልዕክትም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያና ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የኩዌቱ ኤሚር ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸው ታውቋል።