ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኮሚሽነር ኔቨን ሚሚካ ጋር ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ህብረቱ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነሩ አረጋገጠዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት መንግስት እያካሄደ ላለው ማሻሻያ የሚያደርገውን ድጋፍ በተመሳሳይ እንደሚያጠናክር መገለፁን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት 㝕የተገኘው መረጃ ያመላክታል።