የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የጸጥታ ሥራ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወሰነ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የጸጥታ ሥራ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወሰነ

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ሁሉም ዞኖች፣ ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና ልዩ ወረዳዎች የጸጥታ ሥራው በፌዴራልና በጸጥታ ሃይል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ መወሰኑ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በአንዳንድ አካባቢዎች በተከሰቱ የጸጥታ ችግሮች፤ የህግ የበላይነት በአግባቡ እንዳይከበር እንቅፋት መሆኑና የዜጎች ደህንነት ጥያቄ ላይ በመውደቁ የክልሉ መንግስት በጠየቀው መሰረት ከሐምሌ 15/2011 ዓ.ም ጀምሮ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ የፌዴራል የፀጥታ ምክር ቤት ወስኗል።

 

በክልሉ በተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ ምክንያት በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ፣ ያልተፈቀዱ ሰልፎችና የክልሉን ፀጥታ የሚያውኩ እንቅስቃሴዎች እንደሚስተዋሉም በመግለጫው የተጠቀሰው።

ስለሆነም በክልሉ ሰላምና ደህንነት ለማስፈን እንዲሁም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲቻልም ከሐምሌ 15/2011 ዓ.ም ጀምሮ ክልሉ በፌዴራልና በፀጥታ ሃይል ቁጥጥር ሥር ሆኖ በጊዜያዊ በኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወስኗል።

ዝርዝሩ በቀጣይ ይፋ እንደሚሆንም ተገልጿል። ዘገባው የደቡብ መገናኛ ብዙሃን ነው።